13 ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል።
14 በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?
15 የአስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይገበያል፤የጠቢብም ጆሮ አጥብቆ ይሻታል።
16 እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።
17 አስቀድሞ ጒዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።
18 ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።
19 የተበደለ ወንድም ከተመሸገ ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤ጠቡም እንደ ጠንካራ የግንብ መዝጊያ ነው።