2 ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።
3 ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች።
4 ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።
5 ለክፉ ሰው ማድላት፣ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።
6 የተላላ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤አፉም በትር ይጋብዛል።
7 ተላላ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።
8 የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጣዊ ክፍል ዘልቆ ይገባል።