1 ልጄ ሆይ፤ ቃሌን ብትቀበል፣ትእዛዜንም በልብህ ብታኖር፣
2 ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ልብህንም ወደ ማስተዋል ብትመልስ፣
3 እንዲሁም የመለየት ጥበብን ብትማጠን፣ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማስተዋልን ብትጣራ፣
4 እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት፣እንደ ተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣
5 በዚያን ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ።
6 እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል።