16 ከአመንዝራ ሴትም ትጠብቅሃለች፤በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ታድንሃለች፤
17 ይህችም የልጅነት ባሏን የተወች፣በአምላኳ ፊት የገባችውን ኪዳን ያቃለለች ናት።
18 ቤቷ ወደ ሞት ያደርሳል፤መንገዷም ወደ መናፍስተ ሙታን ያመራል።
19 ወደ እርሷ የሚገባ ማንም አይመለስም፤የሕይወትንም መንገድ አያገኝም።
20 አንተም በደጋግ ሰዎች ጐዳና ትሄዳለህ፤የጻድቃንንም መንገድ ይዘህ ትጓዛለህ።
21 ቅኖች በምድሪቱ ይቀመጣሉና፤ነቀፋ የሌለባቸውም በእርሷ ላይ ጸንተው ይኖራሉ።
22 ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይወገዳሉ፤ታማኝነት የጐደላቸውም ከእርሷ ይነቀላሉ።