5 በዚያን ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ።
6 እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል።
7 እርሱ ለቅኖች ድልን ያከማቻል፤ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤
8 የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል።
9 በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤
10 ጥበብ ልብህ ውስጥ ትገባለችና፤ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፤
11 የመለየት ችሎታ ይጋርድሃል፤ማስተዋልም ይጠብቅሃል።