1 የወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤በእነዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም።
2 የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤የሚያስቈጣውም ሰው ሕይወቱን ለመከራ ይዳርጋል።
3 ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ተላላ ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።
4 ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤አንዳችም አያገኝም።