3 ከጠብ መራቅ ለሰው ክብሩ ነው፤ተላላ ሁሉ ግን ለጥል ይቸኵላል።
4 ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤አንዳችም አያገኝም።
5 የሰው ልብ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል።
6 ብዙ ሰው ጽኑ ፍቅር እንዳለው ይናገራል፤ታማኝን ሰው ግን ማን ሊያገኘው ይችላል?
7 ጻድቅ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት ይመራል፤ከእርሱም በኋላ የሚከተሉት ልጆቹ ቡሩካን ናቸው።
8 ንጉሥ ለፍርድ ዙፋኑ ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ክፉውን ሁሉ በዐይኖቹ አበጥሮ ይለያል።
9 ለመሆኑ፣ “ልቤን በንጽሕና ጠብቄአለሁ፤ንጹሕ ነኝ፤ ኀጢአት የለብኝም” የሚል ማን ነው?