1 የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤እርሱም እንደ ቦይ ውሃ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል።
2 ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።
3 ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።
4 ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።