12 ጻድቁ የክፉዎችን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ክፉዎችንም ያጠፋቸዋል።
13 ሰው የድኾችን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን ቢዘጋ፣እርሱም ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።
14 በስውር የተደረገ ስጦታ ቊጣን ያበርዳል፤በጒያ የተሸሸገ እጅ መንሻም ታላቅ ቊጣን ጸጥ ያደርጋል።
15 ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሰኘዋል፤ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።
16 የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣በሙታን ጉባኤ ያርፋል።
17 ቅንጦትን የሚወድ ይደኸያል፤የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድም ባለጠጋ አይሆንም።
18 ክፉ ሰው ለጻድቅ፣ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።