15 ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሰኘዋል፤ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።
16 የማስተዋልን መንገድ የሚስት ሰው፣በሙታን ጉባኤ ያርፋል።
17 ቅንጦትን የሚወድ ይደኸያል፤የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድም ባለጠጋ አይሆንም።
18 ክፉ ሰው ለጻድቅ፣ወስላታም ለቅን ሰው ወጆ ይሆናል።
19 ከጨቅጫቃና ከቊጡ ሚስት ጋር ከመኖር፣በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
20 በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ተላላ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።
21 ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤ሕይወትን ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።