2 ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።
3 ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።
4 ትዕቢተኛ ዐይን፣ እብሪተኛ ልብ፣የክፉዎችም መብራት ኀጢአት ናቸው።
5 የትጒህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።
6 በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣በኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።
7 ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤ቅን ነገር ማድረግ አይወዱምና።
8 የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።