5 የትጒህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።
6 በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣በኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።
7 ክፉዎችን ዐመፃቸው ይጠራርጋቸዋል፤ቅን ነገር ማድረግ አይወዱምና።
8 የበደለኛ መንገድ ጠማማ ነው፤የንጹሕ ሰው ጠባይ ግን ቀና ነው።
9 ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣በጣራ ላይ ጥግ ይዞ መኖር ይሻላል።
10 ክፉ ሰው ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ባልንጀራውም ከእርሱ ዘንድ ርኅራኄን አያገኝም።
11 ፌዘኛ ሲቀጣ፣ አላዋቂ ጥበብን ያተርፋል፤ጠቢብ ሰው ቢማር ዕውቀትን ያገኛል።