13 ሰነፍ፣ “አንበሳ ውጪ አለ፤መንገድ ላይ እገደላለሁ” ይላል።
14 የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጒድጓድ ነው፤ እግዚአብሔር የተቈጣውም ይገባበታል።
15 ሞኝነት በሕፃን ልብ ታስሮአል፤የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቅለታል።
16 ሀብቱን ለማካበት ድኻን የሚበድል፣ለባለጠጋም ስጦታ የሚያቀርብ፣ ሁለቱም ይደኸያሉ።
17 የጠቢባንን ቃል ልብ ብለህ ስማ፤ልብህም ወደ ትምህርቴ ያዘንብል፤
18 በልብህ ስትጠብቃቸው፣ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ የተዘጋጁ ሲሆኑ ደስ ይላልና።
19 ስለዚህ እምነትህ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን፣ዛሬ አንተን ራስህን አስተምርሃለሁ።