7 ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።
8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤የቊጣውም በትር ይጠፋል።
9 ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ምግቡን ከድኾች ጋር ይካፈላልና።
10 ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤ጥልና ስድብም ያከትማል።
11 የልብ ንጽሕናን ለሚወድና ንግግሩም ሞገስ ላለው ሰው፣ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።
12 የእግዚአብሔር ዐይኖች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤የማይታመኑትን ሰዎች ቃል ግን እርሱ ከንቱ ያደርጋል።
13 ሰነፍ፣ “አንበሳ ውጪ አለ፤መንገድ ላይ እገደላለሁ” ይላል።