1 ከገዥ ጋር ለመብላት በምትቀመጥበት ጊዜ፣በፊትህ ያለውን በሚገባ አስተውል፤
2 ስግብግብም ብትሆን እንኳ፣በጒሮሮህ ላይ ካራ አጋድምበት፤
3 የእርሱ ጣፋጭ መብል አያስጐምጅህ፤ምግቡ አታላይ ነውና።
4 ሀብት ለማግኘት ስትል ራስህን አታድክም፤ሐሳብህን የመግታት ጥበብ ይኑርህ።
5 በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፤ወዲያው ይጠፋል፤ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበራል፤
6 የስስታምን ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤
7 ሁል ጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤“ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።