24 የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ጠቢብ ልጅ ያለውም በእርሱ ሐሤት ያደርጋል።
25 አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።
26 ልጄ ሆይ፤ ልብህን ስጠኝ፤ዐይኖችህም ከመንገዴ አይውጡ፤
27 ዘልዛላ ሚስት ጠባብ ጒድጓድ፣አመንዝራም ሴት ዐዘቅት ናትና፤
28 እንደ ወንበዴ ታደባለች፤በሰዎችም መካከል ወስላቶችን ታበዛለች።
29 ዋይታ የማን ነው? ሐዘንስ የማን ነው?ጠብ የማን ነው? ብሶትስ የማን ነው?በከንቱ መቊሰል የማን ነው? የዐይን ቅላትስ የማን ነው?
30 የወይን ጠጅ በመጠጣት ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ነው፤እየዞሩ ድብልቅ የወይን ጠጅ ለሚቀማምሱ ሰዎች ነው።