5 በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፤ወዲያው ይጠፋል፤ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበራል፤
6 የስስታምን ምግብ አትብላ፤ጣፋጭ መብሉም አያስጐምጅህ፤
7 ሁል ጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤“ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም።
8 የበላሃት ትንሿ እንኳ ታስመልስሃለች፤የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ።
9 ከጅል ጋር አትነጋገር፤የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና።
10 የጥንቱን የወሰን ምልክት አታፋልስ፤አባት የሌላቸውንም ልጆች መሬት አትግፋ፤
11 ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፤እርሱ ይፋረድላቸዋል።