1 እነዚህ የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዷቸው ሌሎች የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፦
2 ነገርን መሰወር ለእግዚአብሔር ክብሩ ነው፤ነገርን ፈልፍሎ ማውጣት ግን ለነገሥታት ክብራቸው ነው።
3 ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ፣የነገሥታትም ልብ እንደዚሁ አይመረመርም።
4 ከብር ዝገትን አስወግድ፤አንጥረኛውም ንጹሕ ነገር ያገኛል፤