24 ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር፣በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
25 ከሩቅ የሚመጣ መልካም ዜና፣የተጠማችን ነፍስ እንደሚያረካ ቀዝቃዛ ውሃ ነው።
26 ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣እንደ ደፈረሰ ምንጭ ወይም እንደ ተበከለ የጒድጓድ ውሃ ነው።
27 ከመጠን በላይ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም።