6 በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤በታላላቆች መካከል መገኘትም አይመርህ፤
7 በትልቅ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ፣ራሱ፣ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና።በዐይንህ ያየኸውን ሁሉ፣
8 ወደ ፍርድ አደባባይ በችኰላ አታውጣው፤ባልንጀራህ ካሳፈረህ፣ኋላ ምን ይውጥሃል?
9 ስለ ራስህ ጒዳይ ከባልንጀራህ ጋር በምትከራከርበት ጊዜ፣የሌላውን ሰው ምስጢር አታውጣ፤
10 ያለዚያ ይህን የሚሰማ ያሳፍርሃል፤አንዴ የጠፋውን ስምህንም ፈጽሞ መመለስ አትችልም።
11 ባግባቡ የተነገረ ቃል፣በብር መደብ ላይ እንደ ተቀረጸ የወርቅ እንኮይ ነው።
12 የጠቢብ ሰው ዘለፋ ለሚሰማ ጆሮ፣እንደ ወርቅ ጒትቻ ወይም እንደ ጥሩ የወርቅ ጌጥ ነው።