1 በረዶ በበጋ፣ ዝናብ በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉ፣ክብርም ለተላላ አይገባውም።
2 ክንፎቿን እንደምታርገበግብ ድንቢጥ ወይም ቱር እንደምትል ጨረባ፣ከንቱ ርግማንም በማንም ላይ አይደርስም።
3 ለፈረስ አለንጋ፣ ለአህያ መሸበቢያ፣ለተላላ ጀርባም በትር ይገባዋል።
4 ቂልን እንደ ቂልነቱ አትመልስለት፤አለዚያ አንተም ራስህ እንደ እርሱ ትሆናለህ።
5 ቂልን እንደ ቂልነቱ መልስለት፤አለዚያ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።
6 በተላላ እጅ መልእክትን መላክ፣የገዛ እግርን እንደ መቊረጥ ወይም ዐመፃን እንደ መጋት ነው።