5 ቂልን እንደ ቂልነቱ መልስለት፤አለዚያ ጠቢብ የሆነ ይመስለዋል።
6 በተላላ እጅ መልእክትን መላክ፣የገዛ እግርን እንደ መቊረጥ ወይም ዐመፃን እንደ መጋት ነው።
7 በቂል አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣ሰላላ የሽባ ሰው እግር ነው።
8 ለተላላ ክብር መስጠት፣በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።
9 በአላዋቂ አንደበት የሚነገር ምሳሌ፣በሰካራም እጅ እንዳለ እሾኽ ነው።
10 ቂልን ወይም የትኛውንም ዐላፊ አግዳሚ የሚቀጥር፣ፍላጻውን በነሲብ እየወረወረ ወገኖቹን እንደሚያቈስል ቀስተኛ ነው።
11 ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ ሁሉ፣ተላላም ቂልነቱን ይደጋግማል።