14 ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣እንደ ርግማን ይቈጠራል።
15 ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥጠፈጠፍ ናት፤
16 እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትንበእጅ እንደ መጨበጥ ነው።
17 ብረት ብረትን እንደሚስል፣ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።
18 በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።
19 ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጦ ያሳያል።
20 ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣የሰውም ዐይን አይረካም።