2 ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን።
3 ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የተላላ ሰው ጒነጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።
4 ንዴት ጨካኝ፣ ቊጣም ጐርፍ ነው፤በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?
5 የተገለጠ ዘለፋ፣ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።
6 ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣የወዳጅ ማቊሰል ይታመናል።
7 ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።
8 ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።