4 ንዴት ጨካኝ፣ ቊጣም ጐርፍ ነው፤በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?
5 የተገለጠ ዘለፋ፣ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።
6 ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣የወዳጅ ማቊሰል ይታመናል።
7 ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።
8 ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።
9 ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።
10 የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።