13 ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምሕረትን ያገኛል።
14 እግዚአብሔርን ዘወትር የሚፈራ ሰው ቡሩክ ነው፤ልቡን የሚያደነድን ግን መከራ ላይ ይወድቃል።
15 ታዳጊ በሌለው ሕዝብ ላይ የተሾመ ጨካኝ ገዥ፣እንደሚያገሣ አንበሳ ወይም ተንደንድሮ እንደሚይዝ ድብ ነው።
16 ጨካኝ ገዥ ማመዛዘን ይጐድለዋል፤ያላግባብ የሚገኝን ጥቅም የሚጸየፍ ግን ዕድሜው ይረዝማል።
17 የሰው ደም ያለበት ሰው፣ዕድሜ ልኩን ሲቅበዘበዝ ይኖራል፤ማንም ሰው አይርዳው።
18 አካሄዱ ነቀፋ የሌለበት ሰው ክፉ አያገኘውም፤መንገዱ ጠማማ የሆነ ግን ድንገት ይወድቃል።
19 መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ከንቱ ተስፋን ይዞ የሚጓዝ ግን ድኽነትን ይወርሳል።