23 ሸንጋይ አንደበት ካለው ይልቅ፣ሰውን የሚገሥጽ ውሎ ዐድሮ ይወደዳል።
24 ከአባት ከእናቱ ሰርቆ፣“ይህ ጥፋት አይደለም” የሚል የአጥፊ ተባባሪ ነው።
25 ስስታም ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል።
26 በራሱ የሚታመን ተላላ ነው፤በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም።
27 ለድኾች የሚሰጥ አይቸገርም፤አይቶአቸው እንዳላየ የሚሆን ግን ብዙ ርግማን ይደርስበታል።