11 ተላላ ሰው ቊጣውን ያለ ገደብ ይለቀዋል፤ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።
12 ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።
13 ድኻውና ጨቋኙ የጋራ ነገር አላቸው፤ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዐይን ብርሃንን ሰጥቶአቸዋል።
14 ንጉሥ ለድኻ ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጥ፣ዙፋኑ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
15 የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
16 ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ኀጢአት ይበዛል፤ጻድቃን ግን የእነርሱን ውድቀት ያያሉ።
17 ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።