4 ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤ጒቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል።
5 ባልንጀራውን የሚሸነግል፣ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።
6 ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።
7 ጻድቅ ለድኾች ፍትሕ ይጨነቃል፤ክፉ ሰው ግን ደንታ የለውም።
8 ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤ጠቢባን ግን ቊጣን ያበርዳሉ።
9 ጠቢብ ሰው ከተላላ ጋር ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣ተላላ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።
10 ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።