10 “አገልጋይን በጌታው ፊት በክፉ አታንሣው፤አለዚያ ይረግምህና ጒዳት ያገኝሃል።
11 “አባቱን የሚረግም፣እናቱን የማይባርክ ትውልድ አለ፤
12 ራሳቸውን ንጹሓን አድርገው የሚቈጥሩ፣ሆኖም ከርኵሰታቸው ያልነጹ አሉ፤
13 ዐይናቸው ትዕቢተኛ የሆነ፣ አስተያያቸው ንቀት የሞላበት፣
14 ድኾችን ከምድር፣ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።
15 “አልቅት ሁለት ሴት ልጆች አሉት፤‘ስጡን! ስጡን!’ እያሉ ይጮኻሉ፤“ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤‘በቃኝን’ ከቶ የማያውቁ አራት ናቸው፤
16 እነርሱም መቃብር፣ መካን ማሕፀን፣ውሃ ጠጥታ የማትረካ ምድር፣‘በቃኝ’ የማይል እሳት ናቸው።