14 ድኾችን ከምድር፣ችግረኞችንም ከሰው ዘር መካከል ለማጥፋት፣ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣መንጋጋቸውም ካራ የሆነ አሉ።
15 “አልቅት ሁለት ሴት ልጆች አሉት፤‘ስጡን! ስጡን!’ እያሉ ይጮኻሉ፤“ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤‘በቃኝን’ ከቶ የማያውቁ አራት ናቸው፤
16 እነርሱም መቃብር፣ መካን ማሕፀን፣ውሃ ጠጥታ የማትረካ ምድር፣‘በቃኝ’ የማይል እሳት ናቸው።
17 “በአባት ላይ የምታፌዝ ዐይን፣የእናትንም ትእዛዝ የምትንቅ፣የሸለቆ ቊራዎች ይጐጠጒጧታል፤ጆፌ አሞሮችም ይበሏታል።
18 “እጅግ የሚያስደንቁኝ ሦስት ነገሮች አሉ፤የማላስተውላቸውም አራት ናቸው፤
19 የንስር መንገድ በሰማይ፣የእባብ መንገድ በቋጥኝ፣የመርከብ መንገድ በባሕር፣የሰውም መንገድ ከሴት ልጅ ጋር ናቸው።
20 “የአመንዝራዪቱ መንገድ ይህ ነው፤በልታ አፏን በማበስ፣‘ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም’ ትላለች።