20 ክንዶቿን ለድኾች ትዘረጋለች፣እጆቿንም ለችግረኞች ፈታ ታደርጋለች።
21 በረዶ ቢጥል ለቤተ ሰዎቿ አትሠጋም፤ሁሉም ቀይ ልብስ ለብሰዋልና።
22 ለመኝታዋ የዐልጋ ልብስ ትሠራለች፤ቀጭን በፍታና ሐምራዊ ልብስ ለብሳለች።
23 ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከልበአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው።
24 የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።
25 ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤መጭውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች።
26 በጥበብ ትናገራለች፤በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።