23 ባሏ በአገር ሽማግሌዎች መካከልበአደባባይ በተቀመጠ ጊዜ የተከበረ ነው።
24 የበፍታ መጐናጸፊያዎችን ሠርታ ትሸጣለች፤ለነጋዴዎችም ድግ ታቀርባለች።
25 ብርታትንና ሞገስን ተጐናጽፋለች፤መጭውን ጊዜ በደስታ ትቀበላለች።
26 በጥበብ ትናገራለች፤በአንደበቷም ቀና ምክር አለ።
27 የቤተ ሰዎቿን ጒዳይ በትጋት ትከታተላለች፤የስንፍና እንጀራ አትበላም።
28 ልጆቿ ተነሥተው፤ ቡርክት ይሏታል፤ባሏም እንዲሁ፤ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤
29 “ብዙ ሴቶች መልካም አድርገዋል፤አንቺ ግን ሁሉንም ትበልጫለሽ።”