5 አለዚያ ጠጥተው የሕጉን ድንጋጌ ይረሳሉ፤የተጨቈኑትን ሁሉ መብት ይገፋሉ።
6 ለሚጠፉት የሚያሰክር መጠጥ፣በሥቃይ ላሉትም የወይን ጠጅ ስጧቸው፤
7 ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።
8 “ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
9 ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”
10 ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል?ከቀይ ዕንቊ እጅግ ትበልጣለች።
11 ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤የሚጐድልበትም ነገር የለም።