7 ጠጥተው ድኽነታቸውን ይርሱ፤ችግራቸውንም ከእንግዲህ አያስቡ።
8 “ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት።
9 ተናገር፤ በቅንነትም ፍረድ፤የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”
10 ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል?ከቀይ ዕንቊ እጅግ ትበልጣለች።
11 ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤የሚጐድልበትም ነገር የለም።
12 በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም።
13 የበግ ጠጒርና የተልባ እግር መርጣ፣ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች።