1 ልጆቼ ሆይ፤ የአባትን ምክር አድምጡ፤ልብ ብላችሁ ስሙ፤ ማስተዋልንም ገንዘብ አድርጉ።
2 በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ።
3 በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣
4 አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤“ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።
5 ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤ቃሌን አትርሳ፤ ከእርሷም ዘወር አትበል።
6 ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች።