12 ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ስትሮጥም አትደናቀፍም።
13 ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።
14 ወደ ኀጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤
15 ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤
16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ ባይናቸው አይዞርም።
17 የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
18 የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።