16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ሰውን ካላሰናከሉ እንቅልፍ ባይናቸው አይዞርም።
17 የክፋት እንጀራ ይበላሉ፤የዐመፅ ወይን ጠጅ ይጠጣሉ።
18 የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
19 የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።
20 ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።
21 ከእይታህ አታርቀው፤በልብህም ጠብቀው፤
22 ለሚያገኘው ሕይወት፤ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።