18 የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ፣ብርሃኑ እየጐላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋጋን ነው።
19 የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም።
20 ልጄ ሆይ፤ የምነግርህን አስተውል፤ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ።
21 ከእይታህ አታርቀው፤በልብህም ጠብቀው፤
22 ለሚያገኘው ሕይወት፤ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።
23 ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤የሕይወት ምንጭ ነውና።
24 ጥመትን ከአፍህ አስወግድ፤ብልሹ ንግግርም ከከንፈሮችህ ይራቅ።