3 በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣
4 አባቴ እንዲህ ሲል አስተማረኝ፤“ቃሌን በሙሉ በልብህ ያዝ፤ትእዛዜንም ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ።
5 ጥበብን አግኛት፤ ማስተዋልን ያዛት፤ቃሌን አትርሳ፤ ከእርሷም ዘወር አትበል።
6 ጥበብን አትተዋት፤ እርሷም ከለላ ትሆንሃለች፤አፍቅራት፤ እርሷም ትጠብቅሃለች።
7 ጥበብ ታላቅ ነገር ናት፤ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፤ያለህን ሁሉ ብታስከፍልህም ማስተዋልን ገንዘብህ አድርጋት።
8 ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤
9 በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።