8 ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤
9 በራስህ ላይ ሞገሳማ አክሊል ትደፋልሃለች፤የክብር ዘውድም ታበረክትልሃለች።
10 ልጄ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ቃሌንም ልብ በል፤የሕይወት ዘመንህም ትበዛለች።
11 በጥበብ ጐዳና አስተምርሃለሁ፤ቀጥተኛውንም መንገድ አሳይሃለሁ።
12 ስትሄድ ርምጃህ አይሰናከልም፤ስትሮጥም አትደናቀፍም።
13 ምክርን አጥብቀህ ያዛት፤ አትልቀቃት፤ጠብቃት፤ ሕይወትህ ናትና።
14 ወደ ኀጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤