17 ለአንተ ብቻ ይሁኑ፤ባዕዳን አይጋሩህ።
18 ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፤በልጅነት ሚስትህም ደስ ይበልህ።
19 እርሷ እንደ ተወደደች ዋላ፣ እንደ ተዋበች ሚዳቋ ናት፤ጡቶቿ ዘወትር ያርኩህ፤ፍቅሯም ሁል ጊዜ ይማርክህ።
20 ልጄ ሆይ፤ በአመንዝራ ሴት ፍቅር ለምን ትሰክራለህ?የሌላዪቱንስ ሴት ብብት ስለ ምን ታቅፋለህ?
21 የሰው መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ ነውና፤እርሱ መሄጃውን ሁሉ ይመረምራል።
22 ክፉውን ሰው የገዛ መጥፎ ሥራው ያጠምደዋል፤የኀጢአቱም ገመድ ጠፍሮ ይይዘዋል።
23 ከተግሣጽ ጒድለት የተነሣ ይሞታል፤ከተላላነቱም ብዛት መንገድ ይስታል።