5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፤ርምጃዎቿም በቀጥታ ወደ ሲኦል ያመራሉ።
6 ስለ ሕይወት መንገድ ደንታ የላትም፤መንገዶቿ ዘወርዋራ ናቸው፤ ለእርሷ ግን አይታወቃትም።
7 እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ከምነግራችሁ ቃል ፈቀቅ አትበሉ።
8 መንገድህን ከእርሷ አርቅ፤በደጃፏም አትለፍ፤
9 ይኸውም ጒብዝናህን ለሌሎች፣ዕድሜህንም ለጨካኞች እንዳትሰጥ ነው፤
10 ባዕዳን በሀብትህ እንዳይፈነጥዙ፣ልፋትህም የሌላውን ሰው ቤት እንዳያበለጽግ ነው።
11 በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ።