7 እንግዲህ፣ ልጆቼ ሆይ፤ አድምጡኝ፤ከምነግራችሁ ቃል ፈቀቅ አትበሉ።
8 መንገድህን ከእርሷ አርቅ፤በደጃፏም አትለፍ፤
9 ይኸውም ጒብዝናህን ለሌሎች፣ዕድሜህንም ለጨካኞች እንዳትሰጥ ነው፤
10 ባዕዳን በሀብትህ እንዳይፈነጥዙ፣ልፋትህም የሌላውን ሰው ቤት እንዳያበለጽግ ነው።
11 በዕድሜህ መጨረሻ ታቃሥታለህ፤ሥጋህና ሰውነትህ ሲከዳህ።
12 እንዲህም ትላለህ፤ “ምነው! ተግሣጽን ጠላሁ፤ልቤስ ምነው! መታረምን ናቀ፤
13 የመምህሮቼን ቃል አልሰማሁም፤አሰልጣኞቼንም አላደመጥኋቸውም፤