2 ትእዛዜን ጠብቅ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ትምህርቴንም እንደ ዐይንህ ብሌን ተንከባከበው።
3 በጣትህ ላይ እሰረው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፈው።
4 ጥበብን፣ “እኅቴ ነሽ” በላት፤ማስተዋልንም፣ “ዘመዴ ነህ” በለው፤
5 ከአመንዝራ ሴት፣በአንደበቷም ከምታታልል ዘልዛላ ሴት ይጠብቁሃል።
6 በቤቴ መስኮት፣በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።
7 ማስተዋል የጐደለውን ወጣት፣ብስለት ከሌላቸው መካከል አየሁት፤ከጎልማሶችም መካከል ለየሁት።
8 የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤