20 በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን አይመለስም።”
21 በሚያግባቡ ቃላት አሳተችው፤በለሰለሰ አንደበቷ አታለለችው።
22 ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ሳያንገራግር ተከተላት፤
23 ፍላጻ ጒበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣በራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ።
24 ልጆቼ ሆይ፤ አሁንም አድምጡኝ፤የምለውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ።
25 ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ፤ወደ ስሕተት ጐዳናዋም አትግቡ።
26 አዋርዳ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤የገደለቻቸውም ስፍር ቊጥር የላቸውም።