1 ጥበብ ጮኻ አትጣራምን?ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አታሰማምን?
2 በመንገድ አጠገብ ባሉ ኰረብቶች፣መንገዶቹ በሚገናኙበትም ላይ ትቆማለች፤
3 ወደ ከተማዪቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣በመግቢያዎቹ ላይ፣ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ ስትል ትጮኻለች፤
4 “ሰዎች ሆይ፤ የምጠራውኮ እናንተን ነው፤ለሰው ልጆች ሁሉ ድምፄን ከፍ አደርጋለሁ።
5 እናንተ ብስለት የጐደላችሁ፤ ጠንቃቃነትን ገንዘብ አድርጉ፤እናንተ ተላሎች፤ ማስተዋልን አትርፉ።