33 ምክሬን አድምጡ፤ ጥበበኞች ሁኑ፤ቸልም አትበሉት።
34 በየለቱ ደጃፌ ላይ የሚጠብቅ፣በበራፌ ላይ የሚጠባበቅ፣የሚያዳምጠኝ ሰው ቡሩክ ነው።
35 የሚያገኘኝ ሁሉ ሕይወትን ያገኛልና፤ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል።
36 የሚያጣኝ ሁሉ ግን ራሱ ይጐዳል፤የሚጠሉኝም ሁሉ ሞትን ይወዳሉ።