1 ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አቆመች፤
2 ፍሪዳዋን አረደች፤ የወይን ጠጇን ጠመቀች፤ማእዷንም አዘጋጀች።
3 ሴት አገልጋዮቿንም ላከች፤ከከተማዪቱም ከፍተኛ ቦታ ተጣራች።
4 እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” አለች።
5 “ኑ፤ ምግቤን ተመገቡ፤የጠመቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
6 የሞኝነት መንገዳችሁን ተዉ፤ በሕይወት ትኖራላችሁ፤በማስተዋልም መንገድ ተመላለሱ።