10 “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፤
11 ዘመንህ በእኔ ምክንያት ይረዝማልና፤ዕድሜም በሕይወትህ ላይ ይጨመርልሃል።
12 ጠቢብ ብትሆን ጥበበኛነትህ ለራስህ ነው፤ፌዘኛ ብትሆን የምትጐዳው ያው አንተው ነህ።”
13 ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት።
14 በቤቷ ደጃፍ ላይ ትጐለታለች፤በከተማዪቱ ከፍተኛ ቦታ በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች።
15 በዚያ የሚያልፉትን፣መንገዳቸውን ይዘው የሚሄዱትን ትጣራለች።
16 እርሷም ማመዛዘን ለጐደላቸው፣“ማስተዋል የሌላችሁ ሁሉ ወደዚህ ኑ” ትላለች።